+251 900 14 14 14/ +251 900 15 15 15

ስለ እኛ/About Us

“ኢትዮጵያን እናክማት!” ፡- በኢፌዲሪ ሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከጥቅምት 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘ እና በቦርድ የሚመራ ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡
“ኢትዮጵያን እናክማት!” ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት፡- በመላው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅንጣት ሰወኛ ልዩነቶች ሳይፈጠሩ የግጭትና የመጨካከን ማዕበልን አጥፍቶ፤ በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ተደቁሳ በጽኑ የታመመችውን ሀገራችንን በደቦ በማከም፤ ፍጹም ሠላም፣ልምላሜ፣ፍቅርና መከባበር የተመላበት ኑሮ የሰፈነባት፣ የሰብአዊነት ተምሳሌት የሆነች፣ የዓለማችን ድንቅ ሀገር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን መሆናችንን በዓለም መድረክ ለማሳየት የሚታትር ተቋም ነው፡፡ ለዚህም ‹‹የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!›› በሚል ኃይለ ቃል የሚከናወኑ የተለያዩ መርሀ-ግብሮችን በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተደራሽ በሚሆን መልኩ ከተለያዩ መንግስታዊና የግል ሀገር በቀል ተቋማት እንዲሁም ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር አሰናድቶ ተፈጻሚ ለማድረግ፤ በመላው ዓለም የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ኑ! ኢትዮጵያን ለማከም ያገረሸባትን ሕመም አስቀድመን በመለየት ሕክምና እንድታገኝ በማድረግ ማገገሚያዋን በጋራ እንፈልግ በማለት በኢትዮጵያነት ክብርና ፍቅር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

Read More...

የቦርድ አባላት/Board Members

ይህ ከተለያየ ዘርፍ በአንጋፋና በወጣት ትኩስ ኃይል ስብጥርነት የተሰባሰበው የቦርድ አባላት፤ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስፋ እንዲሳተፉበትና ኢትዮጵያችንን በጽናት ለማከም አንድ ዓመት ከሥድስት ወራት በላይ መሠረታዊ ጥናት በማድረግ የራሱን ቢሮ በዘመናዊና በዲጂታል መልኩ በማደራጀት ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ምክረ ሀሳብ አሰናድቷል፡፡


‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት በተቋም ደረጃም፡- የራሱን ዲጂታል ስቱዲዮ፣የአይቲ ስታፍ፣የዝግጅትና ፕሮሞሽን ስታፍ፣መጠነኛ የቁሳቁሶች ማከማቻ፣ የዝግጅቶች መድረክ እንዲሁም አጠቃላይ የማኔጅመንት ቢሮ የተዘጋጀለት ሲሆን ፤ በዲጂታል ስቱዲዮ፡- ራሱን የቻለ የሚዲያ ፕላት ፎርም፣ የተለያዩ የቅስቀሳ ሙዚቃዎች፣ዘጋቢ ፊልሞች፣የተለያዩ ዘውግ ያላቸው ማስታወቂያዎች እንዲሁም ይህን/እየተጠቀምንበት የምንገኘውን የሎተሪውን በይነ መረብ/ዌብሳይትን ጨምሮ የተለያዩ በርካታ ቅድመ ሥራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡

‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት ቀጣይነት ባለው ኢትዮጵያን ለማከም የአምስት ዓመት ዕቅድ መሠረት ከሦስት መቶ በላይ ሰብአዊነት የሚሰማቸውን በጎ ፈቃደኛ አባላትን አቅፎ በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም እየተዘዋወረ የኃብት ማሰባሰብና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀራርቦ ችግሮቻችንን በማስወገድ በተለያዩ ጉዳዮች በጽኑ የታመመችውን ኢትዮጵያችንን በአብሮነት ተደጋግፈን በማከም አመርቂ ውጤት ለማምጣት ቅድመ ዝግጅቶችን በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡ እርስዎና ቤተሰብዎም ኢትዮጵያን ለማከም ስለምታግዙን በኢትዮጵያዊነት ክብርና ፍቅር ሠላምና ክብረት ይስጥልን፡፡

ይተኮር፡- የ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት አመራሮች በ ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ ሲሆን፤ በዘር፣በጎሳ፣ በኃይማኖት፣በፖለቲካ፣በወገንተኝነት፣ ባጠቃላይ በራስወዳድነትና በክፋት ሠንሰለት ያልተተበተቡ ሲሆን ሰውነትን በማስቀደም ለወገንና ለሀገር ፈጥኖ ደራሽ ሆነው ‹‹የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!›› በሚል ኃይለ ቃል በታማኝነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

ደበበ እሸቱ

የጥበብ ሰው

ደራርቱ ቱሉ

አትሌት

ኡዝታስ አቡበከር አህመድ

የኢስላሚክ ጥናቶች ምሁር