+251 900 14 14 14/ +251 900 15 15 15

ስለ እኛ/About Us

“ኢትዮጵያን እናክማት!” ፡- በኢፌዲሪ ሲቪል ሶሳይቲ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከጥቅምት 16/2015 ዓ.ም ጀምሮ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘ እና በቦርድ የሚመራ ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡
“ኢትዮጵያን እናክማት!” ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት፡- በመላው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅንጣት ሰወኛ ልዩነቶች ሳይፈጠሩ የግጭትና የመጨካከን ማዕበልን አጥፍቶ፤ በተለያዩ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ተደቁሳ በጽኑ የታመመችውን ሀገራችንን በደቦ በማከም፤ ፍጹም ሠላም፣ልምላሜ፣ፍቅርና መከባበር የተመላበት ኑሮ የሰፈነባት፣ የሰብአዊነት ተምሳሌት የሆነች፣ የዓለማችን ድንቅ ሀገር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን መሆናችንን በዓለም መድረክ ለማሳየት የሚታትር ተቋም ነው፡፡ ለዚህም ‹‹የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!›› በሚል ኃይለ ቃል የሚከናወኑ የተለያዩ መርሀ-ግብሮችን በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተደራሽ በሚሆን መልኩ ከተለያዩ መንግስታዊና የግል ሀገር በቀል ተቋማት እንዲሁም ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር አሰናድቶ ተፈጻሚ ለማድረግ፤ በመላው ዓለም የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ኑ! ኢትዮጵያን ለማከም ያገረሸባትን ሕመም አስቀድመን በመለየት ሕክምና እንድታገኝ በማድረግ ማገገሚያዋን በጋራ እንፈልግ በማለት በኢትዮጵያነት ክብርና ፍቅር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

Read More...

የቦርድ አባላት/Board Members

ይህ ከተለያየ ዘርፍ በአንጋፋና በወጣት ትኩስ ኃይል ስብጥርነት የተሰባሰበው የቦርድ አባላት፤ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስፋ እንዲሳተፉበትና ኢትዮጵያችንን በጽናት ለማከም አንድ ዓመት ከሥድስት ወራት በላይ መሠረታዊ ጥናት በማድረግ የራሱን ቢሮ በዘመናዊና በዲጂታል መልኩ በማደራጀት ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ምክረ ሀሳብ አሰናድቷል፡፡


‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት በተቋም ደረጃም፡- የራሱን ዲጂታል ስቱዲዮ፣የአይቲ ስታፍ፣የዝግጅትና ፕሮሞሽን ስታፍ፣መጠነኛ የቁሳቁሶች ማከማቻ፣ የዝግጅቶች መድረክ እንዲሁም አጠቃላይ የማኔጅመንት ቢሮ የተዘጋጀለት ሲሆን ፤ በዲጂታል ስቱዲዮ፡- ራሱን የቻለ የሚዲያ ፕላት ፎርም፣ የተለያዩ የቅስቀሳ ሙዚቃዎች፣ዘጋቢ ፊልሞች፣የተለያዩ ዘውግ ያላቸው ማስታወቂያዎች እንዲሁም ይህን/እየተጠቀምንበት የምንገኘውን የሎተሪውን በይነ መረብ/ዌብሳይትን ጨምሮ የተለያዩ በርካታ ቅድመ ሥራዎች በመሰራት ላይ ናቸው፡፡

‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት ቀጣይነት ባለው ኢትዮጵያን ለማከም የአምስት ዓመት ዕቅድ መሠረት ከሦስት መቶ በላይ ሰብአዊነት የሚሰማቸውን በጎ ፈቃደኛ አባላትን አቅፎ በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም እየተዘዋወረ የኃብት ማሰባሰብና በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተቀራርቦ ችግሮቻችንን በማስወገድ በተለያዩ ጉዳዮች በጽኑ የታመመችውን ኢትዮጵያችንን በአብሮነት ተደጋግፈን በማከም አመርቂ ውጤት ለማምጣት ቅድመ ዝግጅቶችን በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡ እርስዎና ቤተሰብዎም ኢትዮጵያን ለማከም ስለምታግዙን በኢትዮጵያዊነት ክብርና ፍቅር ሠላምና ክብረት ይስጥልን፡፡

ይተኮር፡- የ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ፕሮጀክት አመራሮች በ ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት የሚያገለግሉ ሲሆን፤ በዘር፣በጎሳ፣ በኃይማኖት፣በፖለቲካ፣በወገንተኝነት፣ ባጠቃላይ በራስወዳድነትና በክፋት ሠንሰለት ያልተተበተቡ ሲሆን ሰውነትን በማስቀደም ለወገንና ለሀገር ፈጥኖ ደራሽ ሆነው ‹‹የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!›› በሚል ኃይለ ቃል በታማኝነት የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

ደበበ እሸቱ

የጥበብ ሰው

ደራርቱ ቱሉ

አትሌት

ኡዝታስ አቡበከር አህመድ

የኢስላሚክ ጥናቶች ምሁር

ዓላማ/PURPOSE

01

ዘርፈ ብዙ ሀገራዊና ወገናዊ የሕይወት እክሎች፤ በተለይ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ በሚከሰቱ ጉዳቶች ሳቢያ የሰዎች ሞትና የንብረት ውድመቶችን ለመቅረፍ፤ መሠረታዊ ጥናቶችን ከነ ብልሀታዊ አተገባበራቸው በማሰናዳት ኢትዮጵያን ማከም፡፡

02

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም በተለያዩ የእውቀትና የሙያ ዘርፎች ተክነው፤በፍርሀትና በዝምታ ውስጥ ተሸፍነው ያሉ በሰብአዊነት የታነጹ ቅን የሀገር ባለውለተኞችን አፈላልጎ ወደመድረክ በማምጣት ፤ በሀገራዊና በወገናዊ ግጭቶቻችን ላይ ስር ነቀል የሠላም ማስፈኛ መፍትሔ መዘየድ እንዲችሉ ማድረግ፡፡ ለዚህም በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ የእውቀትና የልምድ ቅብብሎሽ እንዲኖር በማድረግ ትውልድን እየታደጉ በሠላም እጦት የታመመችውን ኢትዮጵያችንን ማከም፡፡ ይሕም፡- በተለያዩ ዘርፎች በአስተምሮት፣በልምድ ልውውጥ፣አዳዲስ መንገዶችን በማመላከት ወ.ዘ.ተ

03

በግጭቶች ሳቢያ በተለያዩ ክልሎች ተፈናቃይ የሆኑና በዳስ ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖቻችን የፈረሰባቸውን ቀዬና ጎጆ ከቀድሞ በተሻለና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በመገንባትና የኢኮኖሚ ድጋፍ በማድረግ ወደቀደመ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ማድረግ፡፡ ይህም፡-በመላው ዓለም የምንኖር ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር፤ የገንዘብ፣ የተለያዩ የሕክምና መገልገያዎችን፣ የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን፣ የተለያዩ መጽሐፍትን ፣ የተለያዩ አልባሳትና መጫሚያዎችን አሰባስቦ በአፋጣኝና በቀጥታ ለተጎጂዎች እንዲዳረስ ማድረግ፡፡

04

አፋጣኝ የሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ቅድሚያ በመስጠት፤ ሕጻናት፣ ሴቶች፣ አዛውንት ወገኖቻችን ከደረሰባቸው የስነ - ልቦና ቀውስ የሚላቀቁበትን የማነቃቂያ መርሀ - ግብሮችን መዘርጋት፡፡

05

በግጭቶቹ የወደሙትንና ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተ እምነቶችን መገንባት፡፡

06

በግጭቶቹ መስዋዕት ለሆኑት ንጹሀን ኢትዮጵያውያንና ለሉአላዊነት አስከባሪው መከላከያ ሠራዊትና ጥምር ጦሩ/ለጀግናው/ዋ ወቶ አደሩ/ሯ መታሰቢያ የሚሆን የጦርነት ቀጠና በነበሩት ክልሎች በቀጣይም በሌሎች ክልሎች በኢትዮጵያ ልዩ የሆነ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠት የሚችል በ ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት›› ስም አዲስ ሆስፒታል መገንባት፡፡

ሰብአዊ ድጋፍ/HUMANITARIAN SUPPORT

የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍ ከሚደረግባቸው ዘርፎች መካከል

በገንዘብ

ገንዘብ የማሰባበብ ዘመቻ

በሕክምና ቁሳቁስና መድሃኒቶች

የሕክምና ቁሳቁስና መድሃኒቶች ከመላው ዓለም የማሰባሰብ ዘመቻ

በመጽሐፍት

ከመላው ዓለም በመጽሐፍት የማሰባሰብ ዘመቻ

በትምህርት ቁሳቁስ

የትምህርት ቁሳቁስ ከመላው ዓለም የማሰባሰብ ዘመቻ

በአልባሳትና መጫሚያዎች

አልባሳትና መጫሚያዎችን ከመላው ዓለም የማሰባሰብ ዘመቻ

ሎተሪ/LOTTERY

ውድ ኢትዮጵያውያን በዚህ ሰዓት በኢትዮጵያ ሀገራችን በተለያዩ ግጭቶችና በተፈጥሮ አደጋዎች ሳቢያ ከ26 ሚሊያን በላይ ወገናችን፤ የሚበላውና የሚጠጣው አጥቶ በሰቀቀን ተኮራምቶ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ሕክምና ለማግኘት የጤና ተቋማት ሳይቀር ወድመዋል፡፡ በመሆኑም በመላው ዓለም ላይ የምንኖር ኢትዮያውያን ‹‹የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!›› በሚል ኃይለ ቃል፤ የትኛውም የውጪ ድርጅት እርዳታ ሳያስፈልገን የራሳችንን ሕመም በራሳችን ልዩነት ሳይከፋፍለን ተደጋግፈን ማከም እንድንችል፤ሁላችንም ይህን ሽልማት የሚያስገኘውን ሎተሪ በመግዛት የነፍስ በረከት እንድናገኝ በኢትዮጵያዊነት ፍቅርና ክብር ‹‹ኢትዮጵያን እናክማት!›› ሰብአዊ እና በጎ አድራጎት ድርጅት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ ለዚህም ባላችሁበት እንደደገፋችሁን ፈጣሪ ይደግፋችሁ፡፡

ለዚህም ‹‹የኢትዮጵያን ሕመም ኢትዮጵያውያን ያክሙታል!›› በሚል ኃይለ ቃል የሚከናወኑ የተለያዩ መርሀ-ግብሮችን በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተደራሽ በሚሆን መልኩ ከተለያዩ መንግስታዊና የግል ሀገር በቀል ተቋማት እንዲሁም ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር አሰናድቶ ተፈጻሚ ለማድረግ፤ በመላው ዓለም የምትኖሩ ውድ ኢትዮጵያውያን ኑ! ኢትዮጵያን ለማከም ያገረሸባትን ሕመም አስቀድመን በመለየት ሕክምና እንድታገኝ በማድረግ ማገገሚያዋን በጋራ እንፈልግ በማለት በኢትዮጵያነት ክብርና ፍቅር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

መዋዕለ ዜና/ NEWS

Here are the news

ዜና 1

ዜና1

ዜና 2

ዜና 2

ዜና 3

ዜና 3

ዜና 4

ዜና 5

ዜና 5

ቀጥታ ስርጭት/LIVE STREAMING

ድጋፍ ሰጪ ተቋማት

ዘ ኢትዮጵያውያን ዲጂታል ስቱዲዮ

ዘ ኢትዮጵያውያን ግሎባል ቴክኖሎጂ

ዘ ኢትዮጵያውያን ግሎባል ማኔጂንግ

ዘ ኢትዮጵያውያን

እንገናኝContact Us

You can contact us

Location:

Inside Ghion Hotel, Demera House, Addis Ababa,Ethiopia

Email:

ethiopianenakmat@gmail.com
ethiopiansthe@gmail.com

Call:

+251 900 14 14 14
+251 900 15 15 15

Loading
Your message has been sent. Thank you!